አለምአቀፍ የክፍያ ስርዓት

አለምአቀፍ የክፍያ ስርዓት

ዘመን ባንክ አለምአቀፍ የክፍያ ስርዓት ደንበኞች ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ሲላክላቸው፣የአገልግሎት ክፍያዎችን፣ የንግድ ክፍያዎችን እና የተለያዩ ክፍያዎችን በፍጥነት እንዲደርሳቸው ያስችላል፡፡

በዘመን ባንክ ወደ ውጪ ሃገራት የሚፈጽሙዋቸውን ክፍያች በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ፡፡ ዘመንን መምረጦ የሚከተሉትን ጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችሎታል፡፡

የባንክ ዋስትና

ይህ አገልግሎት ዘመን ባንክ በዋስትናው ውል መሠረት ደንበኛ ለሦስተኛ ወገን ያለውን የንግድ ሥራ ግዴታ ክፍያ ሳይወጣ ሲቀር ባንኩ ለደንበኛው የውሉን ክፍያ የሚከፍልበት አሰራር ነው፡፡

ደንበኞች ከዘመን ባንክ ጋር በመስራታቸው እነዚህን(ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ) የባንኩ የውጪ ዋስትና አማራጮች ያገኛሉ፡፡

የጨረታ/የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ይህ ዋስትና  በተጫራቹ ጥያቄ መሰረት በጨረታ ወቅት ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ታውቆ ነገርግን ተጫራቹ ከጨረታው ቢወጣ ወይም አሸናፊ መሆኑን መቀበል ባይችል ባንኩ የተጫራቹን ግዴታ የሚወጣበት ነው፡፡

የሥራ አፈጻጸም ዋስትና

የሥራ አፈጻጸም ዋስትና ዘመን ባንክ ለገዢው (ተጠቃሚ) በሻጩ ላይ የሚቀርበውን ማንኛውንም ከአቅርቦት ጉድለት ወይም ከውል የገባውን ግዴታ ካለመወጣት የሚነሱ ጥያቄዎችን  ለማረጋገጥ የሚቀርብ ነው።

የቅድመ ክፍያ ዋስትና

በዚህ ዋስትና ዘመን ባንክ  ገዥዎች ለሻጮች የሚያከናውኑትን ቅድመ ክፍያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ያረጋግጣል።

የጉምሩክ ዋስትና

ይህ ዋስትና ለዘመን ባንክ ደንበኞች ወደ ኢትዮጵያ ከሚያስገቡዋቸው አቅርቦቶች ጋር የተያያዙ የኤግዚቢሽን/የንግድ ትርዒትእና ለሠርቶ ማሳያ የሚሆን ናሙና ጋር በተያያዘ ተመቻችቷል።