ዲጂታል ባንኪንግ

ዲጂታል ባንኪንግ

የዲጂታል ባንኪንግ አቅርቦታችን በሞባይልና በበይነመረብ ባንኪንግ የላቀ አገልግሎት የምንሰጥበት ነው፡፡ 

ደንበኞች በቀላሉ እንዲጠቀሙና ራሳቸውን ችለው የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

የኢንተርኔት ባንኪንግ

የዘመን ባንክ የኢንተርኔት ባንኪንግ ለመጠቀም ቀላልና የግል ሂሳብዎን እንዲከታተሉ ይረዳዎታል።   እንዲሁም የሂሳብ መረጃዎን በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀናት ለማግኘት ምቹ ነው። ፈጣን፣ ነፃ እና ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። የእኛ የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎታችን ለደንበኞች የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣል፡

ኤቲኤም እና የክፍያ መፈጸሚያ ማሽኖች (ፖስ)

ኤቲኤም እና የክፍያ መፈጸሚያ ማሽኖች /ፖስ/ : ዘመን ባንክ ለደንበኞቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ምቹ ለማድረግ በመላው ሀገሪቱ ኤቲኤሞች እና የክፍያ መፈጸሚያ ማሽኖችን  በተለያዩ የንግድ ቦታዎች ላይ በማስቀመጥ ቀላል እና እንከን የለሽ  የክፍያ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል ።

የዘመን ባንክ ኤቲኤም እና የክፍያ መፈጸሚያ ማሽኖች /ፖስ/ የሁሉንም ባንክ ካርዶች እንዲሁም የቪዛ እና የማስተርካርድ ካርዶችን መቀበል ይችላሉ፡፡

ካርድ አልባ

ሁሉም የዘመን ፖስ ማሽኖችና አብዛኛዎቹ ኤቲኤሞች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ወጥቶባቸው በዘመናዊ መንገድ የቀረቡ በመሆናቸው ያለ ንኪኪ ማስተር ካርድና ሌሎች ካርዶችን ይቀበላሉ፡፡

ማስተር ካርድ እና ቪዛ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ንክኪ አልባ ማስተር ካርድ ይገልገሉ

ኤቲኤም እና ፖስ

የPOS እና የኤቲኤም አገልግሎቶችን ለመክፈልም ይጠቀሙ። በአሁኑ ወቅት ከ300 በላይ ኤቲኤም እና 100+POSs በመላ አዲስ አበባ እና በተመረጡ የክልል ከተሞች ይገኛሉ።

የሞባይል ባንኪንግ

በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ ሆነው የዘመን ባንክ ሂሳብዎትን ማየት ቢፈልጉ በተሻሻሉት በስልክዎ በአንድሮይድ ውይም በአይኦኤስ ላይ በሚገኘው የዘመን ባንክ መተግበሪያ በቀላሉ ሂሳብዎትን ማየትና ማንቀሳቀስ ይችላሉ፡፡

በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኘው የዘመን ባንክ አገልግሎት ማዕከል በመሄድ የአጭር ቁጥር አገልግሎት በመመዝገብ እና በስልክዎ ወደ *844# በመደወል አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

*844#

የዴቢት ካርዶች

የዘመን ዴቢት ካርዶች 24 ሰዓት ሙሉ በሂሳብዎ እንዲገለገሉ ያደርጋል። የዘመን ንክኪ የሌለው ዴቢት ካርድ ከኤቲኤም ካርድ በላይ ነው፤ ይህም POS ተርሚናል በኦንላይን ግብይት እና በኤቲኤም ላይ ያለ ጥሬ ገንዘብ ግብይቶችን እንዲያደርጉ ያስችልዎታል። መሰረታዊ የግል ፕሪስቲጅ እና የዜድ ክለብ ዴቢት ካርዶችን እናቀርባለን።

የደመወዝ ክፍያ ካርዶች

ዘመናዊ የንግድ ድርጅቶችን ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጀው የደመወዝ ካርዳችን የሠራተኞችን ደመወዝ በደመወዝ ካርዳቸው በኩል በማሰራጨት አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል 

የቅድመ ክፍያ ካርዶች

በዘመን ባንክ የቅድመ ክፍያ ካርድ አማካኝነት በየቀኑ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጡ ሙሉ ቁጥጥር ማድረግ ይችላሉ። በቅድመ ክፍያ ካርድ ላይ ያለው የገንዘብ መጠን ሊከፈል የሚችል ከፍተኛው መጠን ነው። 

የስጦታ ካርዶች

ለዓመት በዓል፣ ለልደት፣ ለክብረ በዓልና ለመሳሰሉት ዝግጅቶች ጥሩ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ? የትኛውንም የባንካችንን ቅርንጫፎች ወይም ወኪሎቻችንን በማነጋገር ይህንን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዘመን ስጦታ በኮርፖሬት ደረጃ ለሠራተኞች፣ ለበዓላትና ለአጋሮች ወዘተ ስጦታ ለመስጠት ሊውል ይችላል፡፡

የዘመን ፕላቲኒየም የጉዞ ቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድ

የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የቅድመ ክፍያና ንክኪ አልባ የጉዞ ካርድ ኢትዮጵያውያን ተጓዦች ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የዩኤስ ዶላር ወይም ዩሮ ምንዛሬዎች እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል ይህ ምርት ደንበኞቻችን በውጭ ሀገራት ለሚያደርጓቸው ጉዞዎች ያለ ጥሬ ገንዘብ እንዲገለገሉ ያደርጋቸዋል፡፡

ዘመን የትምህርት አስተዳደርና ክፍያ ሥርዓት

ምቹ የክፍያ ሥርዓት፡

በየትኛውም ጊዜና ቦታ መረጃ ማግኘት፡

የዲጂታል ሐዋላ አገልግሎት

ዘመን ባንክ በሃገራችን ከሚገኙ ና ዋና የፊንቴክ ኩባንያዎች እና የክፍያ መሣሪያ አቅራቢዎች ጋር በመተባበር የዲጂታል ገንዘብ መላኪያ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ እና ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። ይህ አገልግሎት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኤትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ሌሎች ዜጎች ባሉበት ቦታ በመሆን የማስተር ካርድ ወይም የቪዛ ካርዳቸውን በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ገንዘብ በቀላሉ  እንዲልኩ ያስችላቸዋል።

Reach us at