ቅድመ-ገፅ » ዲጂታላይዜሽን እና አጋርነት
ዘመን ባንክ በዲጂታላይዜሽን ጉልህ እድገት ማሳየቱን ቀጥሏል። ባንኩ ተደራሽነቱን ለማስፋት፣ አገልግሎቱን ለማዘመን፣ደህንነታቸው የተጠበቁ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እና ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ እያቀረበ ይገኛል፡፡
ከነዚህ ስኬቶች በተጨማሪ ዘመን ባንክ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት እና የተለዩ የዲጂታል ባንኪንግ አማራጮችን በማቅረብ በኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ ነው፡፡ ባንካችን ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ክፍያዎችን በበይነ መረብ ለመፈጸም የሚያስችል ኤም.ፒ.ጂ.ኤስ የተባለ የኢኮሜርስ የክፍያ ማሳለጫ ስርዓት በመዘርጋት በኢትዮጵያ ግምባር ቀደም ነው፡፡
ባንካችን ኢንዱስትሪው ላይ ካሉ የተለያዩ ፊንቴኮች እና የሞባይል ገንዘብ አንቀሳቃሾች ጋር በፈጠረው ትስስር (Integration) ለደንበኞቻችን አማራጭ የክፍያ እና የገንዘብ ማዘዋወሪያ መንገድ ከማስፋቱም በተጨማሪ ዘመን ባንክ በተናጠል ያልደረሰባቸውን ገበያዎች ለመድረስ ረድቶታል፡፡
ዘመን ባንክ ልዩ የሆነ የደንበኞች አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም የተለያዩ የዲጂታል አገልግሎቶችን በነጻ በማቅረብ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት የላቀ እንዲሆን በማድረግ ይታወቃል፡፡ በዚህም ባንካችን የዲጂታል አገልግሎቶቹን ለደንበኞቹ ከክፍያ ነፃ በሆነ ሁኔታ ተደራሽ በማድረጉ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው ባንክ ያደርገዋል።
በመጨረሻም በባንካችን ከሚፈፀሙ ጠቅላላ የገንዘብ ዝውውሮች ውስጥ በዲጂታል የገንዘብ የማስተላለፊያ መንገዶች የሚፈፀሙት ግብይቶች ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱ ሲሆን ደንበኞች በዚህ ረገድ መደበኛ የባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ባንካችን ቅርንጫፎች በመሄድ የሚያጠፉትን ጊዜ እና ገንዘብ በመቀነስ ለደንበኞቻችን ምቹ እና አስተማማኝ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ለማቅረብ ተችሏል፡፡ ይህም የባንካችን ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን በመጠቀም ረገድ ስኬታማ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ያሳያል ።
Oct 31, 2025
Currency ConverterCAD
EUR
GBP
SEK
USD