የሳይበር ደህንነት

የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ

ዘመን ባንክ የደንበኞችን ሚስጥራዊ መረጃዎች ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል። የደንበኞቻችንን አመኔታና መተማመን ማስጠበቅ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው።

ደንበኞች በተንቀሳቃሽ መሣሪያቸው አማካኝነት በኢንተርኔት የባንክ አገልግሎት፣ ክፍያና ግብይት ማካሄድ እየተለመደ መጥቷል። በሞባይል ስልክ ባሉበት ቦታ ሆነው ሂሳብን መመልከት፣ የሞባይል ካሜራን በመጠቀም ቼክን ተቀማጭ ሂሳብ ውስጥ ማስገባት፣ ክፍያን መክፈል፣ ለወዳጅ ዘመድ ገንዘብ ማስተላለፍና ግብይቶችን መፈፀም ተችሏል፡፡ ሆኖም እነዚህ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሚዎች ስማቸውን የሂሳብ ቁጥራቸውን የኢሜይል አድራሻዎቻቸውንና የይለፍ ቃሎቻቸውን የመሳሰሉ ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ስለሚጠይቁ ከሞባይል ክፍያዎችና ከባንኪንግ አገልግሎት ጋር የተዛመዱትን ጥቅሞችን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ማመዛዘን አስፈላጊ ነው 

ደንበኞቻችን የማንነት ስርቆትና የማጭበርበር ሰለባ የመሆን እድልን ለመቀነስ የሚከተሉትን የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች እንዲወስዱ እናበረታታለን-

መለያዎትን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ይተግብሩ:-

ተባብረን ማጭበርበርን በመከላከልና ትክክለኛ እርምጃዎችን በመውሰድ ወደ ደህንነቱ የተጠበቀ የባንክ አገልግሎት መፍጠር እንችላለን ።

የማንነት ስርቆትን መከላከል

ማንነትዎን ማረጋገጥና ግላዊ መረጃዎን መጠበቅ እርስዎ፣ ባንክዎና የግል መረጃዎን የሚያገኙ ሌሎች የንግድ ተቋማትን የጋራ ጥረትን ይጠይቃል።

የሚከተሉትን ምክሮች ተግባራዊ ማድረጋችሁ ወንጀለኞች ማንነታችሁን እንዳይሰርቁ ያደርጋቸዋል፦

ምክሮች

ከኢንተርኔት ውጭ ያሉ ምክሮች