በሀገራችን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ጋር ተያይዞ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በተከናወነው መርሃግብር ላይ ዘመን ባንክን በመወከል አቶ ተዋህዶ ታፈሰ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር ስምምነቱን ተፈራርመዋል። በዚህ አጋርነት፤ ዘመን ባንክ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን የመገምገም፣ በፋይናንሱ ዘርፍ ዘላቂ አጋርነትን ለማስመዝገብና ዓላማውን ለማሳካት የሚያግዙ ብድሮችን በማመቻቸት የበኩሉን ይወጣል፡፡
በዝግጅቱ ወቅት አቶ ተዋህዶ እንደገለፁት ይህ አጋርነት ዘላቂነት ያላቸውን ግቦች ከማሳካት አንፃር ጉልህ ሚና የሚጫወት ሲሆን ዘመን ባንክ በአየር ንብረት ጥበቃ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልፀዋል። ዘመን ባንክ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማትና የወደፊት አረንጓዴ ልማትን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል።




