አዲስ አበባ፣ መስከረም 07፣ 2017 ዓ.ም ዘመን ባንክ የደንበኞችን የምስጋና እና እውቅና ቀን ረዥም ጊዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞቹን እና አጋሮቹን በሸራተን ሆቴል በመሸለም እና እውቅና በመስጠት አከበረ፡፡
በዕለቱም ከ250 በላይ ለሆኑ አብረውት ሲሰሩ ለቆዩ ውድ ደንበኞች እና አጋሮች ማለትም በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአየር ትራንሰፖርት፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ለተሰማሩ እንዲሁም አብረውት ለሚሰሩ ዓለም-አቀፍ ድርጅቶች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ዕውቅና በመስጠት አጠናቋል፡፡
