የዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበርየባለአክሲዮኖች 18ኛ መደበኛ እና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

የተከበራችሁ የዘመን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ህግ አንቀፅ 366/1፣ 367/1 እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀፅ 12.1፣ 12.5፣ 13 እና 14.1 መሰረት የዘመን ባንክ አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች 18ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሲኤምሲ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በዕለቱ
በሚካሄደው ጉባዔ ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

▪ የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ልደታ ክፍል ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤ/ቁ አዲስ (https://www.zemenbank.com)

▪ የአክሲዮን ማህበሩ ምዝገባ ቁጥር – MT/AA/3/0052748/2014

▪ የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ – 14,287,986,000.00

▪ የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ – 15,000,000,000.00

የባለአክሲዮኖች 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

1. እስከ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅና ሪፖርቱን ተቀብሎ ማጽደቅ፣

2. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጥቆማ ማካሄድና መምረጥ፣

3. እ.ኤ.አ. የ2025/26 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፣

4. እ.ኤ.አ. የ2025/26 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ፤ መወያየትና በቀረበው ሪፖርት ላይ ውሳኔ ማሳለፍ፣

5. የባንኩ የውጪ ኦዲተር በጠየቀው የተጨማሪ ሥራ ክፍያ ጥያቄ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

6. እ.ኤ.አ. የ2026/27 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን መሰየምና ክፍያቸውን መወሰን፤

7. ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማን መቀበልና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፣

8. እ.ኤ.አ. በ2025/26 በጀት ዓመት በተገኘ የተጣራ ትርፍ አደላደልን በተመለከተ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

9.እ.ኤ.አ. የ2025/26 ለዳይሬክተሮች ቦርድ ከተጠራ ትርፍ ላይ የሚታሰብ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያ መወሰን እና እ.ኤ.አ. የ2026/27 የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል
ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፡፡

    የባለአክሲዮኖች 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

    1. እ.ኤ.አ እስከ ጁን 30 2026 ድረስ የተፈረሙና ክፍያ ያልተፈጸመባቸውን አክሲዮኖች መሰረዝ፣

    2. የባንኩን የተከፈለ ካፒታል መጠን ብር 14,287,986,000.00 እንዲሆን ተወያይቶ መወሰን፣

    3.ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በ12ኛው የባንኩ ባለአክሲዮኖች አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩን የተከፈለ ካፒታል በተጨማሪ በብር 5,000,000,000 በማሳደግ ወደ 20,000,000,000 ከፍ እንዲል የተወሰነውን ውሳኔ ለማሻሻል በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

      4. የባንኩን ካፒታል ማሳደግ፡፡

      5. የጉርሻ አክሲዮን(bonus shares) በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን

      ማሳሰቢያ

      1.በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት ቀናት በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት 15ተኛ ፎቅ በሚገኘው ፋይናንስ እና ኢንቨስተርስ ግንኙነት መምሪያ በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማኅበሩ በተዘጋጀው የውክልና መስጫ ቅጽ ላይ በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን ለማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

        2.የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን ወይም ማንነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

          3.ድርጅት ባለአክሲዮንን ወክሎ የሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ/የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆኑንና ወይም ድርጅቱን/ማኅበሩን ወክሎ በጉባዔ ላይ ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል ስልጣን ያለው ስለመሆኑ የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የተመዘገበ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳዳሪያ ደንብ ወይም ቃለጉባዔ በማስረጃነት ይዞ መቅረብ አለበት፤ አልያም በባንኩ የውክልና ቅፅ መሰረት ውክልና የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

            4.ለተጨማሪ መረጃ ሰንጋ ተራ፣ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 15ተኛ ፎቅ በሚገኘው ፋይናንስ እና ኢንቨስተርስ ግንኙነት መምሪያ በአካል መቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251-115-54-00-53/66 ላይ መደወል ይችላሉ፡፡

              የዘመን ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

              Share