ቅድመ-ገፅ » ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት
የዘመን ባንክ ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ለደንበኞች በልዩነት የተዘጋጁ እና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ይዟል፡፡ በዘመን ባንክ የገቢና ወጪ ንግድዎን የሚረዱ አዳዲስና ልዩ የንግድ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ማግኘት ያችላሉ፡፡
ከዘመን ባንክ የተለያዩ የማይሻሩ እና የተረጋገጡ የክሬዲት ደብዳቤዎች እና የሀገር ውስጥ እና ወደ ውጭ ለመላክ የክሬዲት ደብዳቤዎች ከተለየ የደንበኞች አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ጋር ያገኛሉ፡፡ ለአለም አቀፍ ንግድዎ የክሬዲት ደብዳቤ ወሳኝ አካል ከሆነ ዘመን ባንክ የእርስዎ ምርጫ ነው።
በዘመን ልዩ የአለምአቀፍ የንግድ አገልግሎቶች ደንበኞች የሚከተሉትን የመሳሰሉ ሰፊ የንግድ ፋይናንስ መርሃግብሮችን መጠቀም ያስችላቸዋል፡፡
በዘመን ባንክ የአለምአቀፍ የክፍያ ስርዓት ደንበኞች ከቤተሰብ ገንዘብ ሲላክላቸው፣ የአገልግሎት ክፍያ፣የንግድ ልውውጥ እና የተለያዩ ክፍያዎች ፈጣን ደረሰኞች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡
የውጪ ክፍያዎቾትንም ሊገምቱት በማይችሉት ፍጥነት እናስተናግዳለን። ዘመንን መምረጦ የሚከተሉትን ጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችሎታል፡፡
ገንዘብዎን በደቂቃ – የተላከልዎትን በፍጥነት
ፈጣን የተለያዩ–ምንዛሪ ማስተላለፍ – ለግልዎ እና ለንግድዎ የውጪ ምንዛሪ ወጪዎችዎን ወደ የትኛውም የዓለማችን ክፍል ዘመን ባንክ ከተለያዩ አለም አቀፍ ባንኮች ጋር ባለው ግንኙነት በመጠቀም ማስተላለፍ
ለማንኛውም የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ዘመን ባንክ የእርስዎ ምርጫ ነው።
የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ – ዋና ዋና የብዙ አገራት ገንዘብዎችን ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአሉበት የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት- ትልቅ የግብይት መጠን ላላቸው ትላልቅ ተቋማት በጥያቄዎቻቸው መሰረት ባሉበት የምንዛሪ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
ይህ የቁጠባ ሂሳብ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የተዘጋጀ ሲሆን ሂሳቡን ለመክፈት የተቀመጡትን መስፈርቶች ለሚያሟሉ በኤምባሲዎች፣ በውጭ ንግድ ማህበረሰብ ፣ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች (በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ምንዛሪ) ለሚከፈላቸው የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ሂሳብ ወለድ የማይታሰብለት እና ቁጠባዎች በውጪ ሃገር ገንዘብ የሚቀመጥበት ነው ፡፡ተጨማሪ ገቢ ገንዘቦች በጉምሩክ ከተገለጸ፣ ከጉዞ ወጪ የሚመለስ ገንዘብ ከሆነ ወይም ነዋሪ ካልሆኑ የውጭ ምንዛሪ እና ከሌሎች በዲያስፖራ ቁጠባ ሒሳቦች የሚተላለፉ እና ከየውጭ አገር ዜጎች ሂሳብ የተወሰዱ ቼኮች ተጨማሪ ገንዘቦችን በውጭ ምንዛሪ ማስገባት ይችላሉ። ክፍያዎችም በኢትዪጵያ ብር መፈፀም ይችላሉ፡፡
በብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ኖቶችን እና የክሬዲት ካርድ/ዴቢት ካርድ/ቅድመ ክፍያ ካርድ እና ክፍያ ለመፈጸም ፈቃድ የተሰጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላኪ፣ነጋዴዎች እና/ወይም ድርጅቶች ይህንን አካውንት የውጪ ምንዛሪያቸውን ይዘው ለመቆየት መክፈት ይችላሉ፡፡ ይህ አካውንት በ USD፣ EUR፣ GBP ወይም ሌላ በብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ሊከፈት ይችላል።
Oct 3, 2025
Currency ConverterSEK
EUR
CAD
GBP
USD