ዘመን ባንክ ከአስፓየር ማይክሮ ፋይናንስ ጋር የስትራቴጂካዊ አጋርነት ፊርማ ተፈራረመ

ዘመን ባንክ እና አስፓየር ማይክሮ ፋይናንስ (በምስረታ ላይ) በፋይናንስ አካታችነት፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና በኢኮኖሚ ልማት ዙሪያ ትብብርን ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ ።

የስትራቴጂካዊ አጋርነቱ ዓላማ የባንክና የገንዘብ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ማስፋት ፣ ዘመናዊ የፋይናንስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና በዲጂታል ፋይናንስ ዙሪያ በጋራ ለመስራትና ተቋማዊ አቅምን ማጎልበት ነው ።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አቶ አዲስ ወልደጨርቆስ የዘመን ባንክ የብድር ቺፍ ኦፊሰር ባንኩ ከአስፓየር ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በቅርበት በመሥራት የባንክ ሥራችንን የሚያጠናክሩ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለመስጠትና ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ዘመናዊነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ አገልግሎቶችን ለማቅረብና ባንኩ የሁሉም ተጠቃሚዎችን እድገት ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ይህ ስምምነት ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሆን በመላ አገሪቱ ለሚገኙ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና እና በተለይም የባንክ አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለመሆንና  የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ መሰረት የሚጥል ነው፡፡

Share