ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) በአዲስ አበባ ባዘጋጀውና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የተወከሉ ተሳታፊዎች ለተገኙበት ኮንፈረንስ ዘመን ባንክ ግንባር ቀደም አጋርነትን አሳየ፡፡

የአፍሪካን አቪዬሽን ደህንነት፣ ተደራሽነትና ኦፕሬሽናል ብቃት ላይ በማተኮር የሚካሄደው ስብሰባ በስካይ ላይት ሆቴል ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በተከፈተበት ወቅት ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፣ አቶ አስራት ታደሰ የሪቴይል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰርና አቶ ሚካኤል ፀጋዬ የኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር በእንግድነት ተገኝተዋል፡፡ ከተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡





