ዘመን ባንክ አጋሮቹ ከሆኑት ከአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) እና ከትሬድና ዴቨሎፕመንት ባንክ (TDB) በድምሩ 85 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ፋሲሊቲ በተሳካ ሁኔታ ማግኘቱን ስንገልጽ በደስታ ነው።
ይህ ፋሲሊቲ ዘመን ባንክ የገቢና ወጪ ንግድ ልውውጦችን በተሻለ መልኩ ለመደገፍ፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች የውጭ ምንዛሪ ተደራሽነትን ለማሻሻልና በተለዋዋጭ ገበያ ውስጥ ባንኩ ለደንበኞች ፍላጎት ቀልጣፋ ምላሽ መስጠት እንዲችል ያግዘዋል፡፡
ዘመን ባንክ የአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) እና ከትሬድና ዴቨሎፕመንት ባንክ (TDB) ባንኩ ላሳዩት እምነትና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
