ቅድመ-ገፅ » የቢዝነስ ብድር
ብድርዎ ቢያስፈልግዎ ዘመን ባንክ ለእርስዎ መፍትሄ አለው፡፡ የሥራ መጀመሪያ ካፒታል፣ የንብረት ፋይናንስ ወይም የፕሮጀክት ማስኬጃ ገንዘብ የሚያስፈልጎት ከሆነ ዘመን ባንክ ለእርስዎ የተዘጋጀና የተሟላ የገንዘብ አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ሁሉም የብድር ውሳኔዎች በባለሙያዎች የታገዘ ፈጣን ምላሽና ለእርስዎ የሚሆኑ መፍትሄዎችን የሚሰጡ ናቸው፡፡
እያንዳንዱ የብድር ጥያቄ መደበኛ የጊዜ ሰሌዳ አለው፡፡ የብድር ጥያቄዎን እንዳስገቡ ዘመን ባንክ የብድር ማመልከቻዎ ተቀባይነት እንዳገኘ የሚገልፅ ደብዳቤ በመስጠት የብድር ሂደቱን ይጀምራል፡፡ በመሆኑም ስለብድርዎ ሂደት ወቅታዊ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ዘመን ባንክ የሥራዎን ዕድገትና የኢንቨስትመንት ግቦችዎን ለመደገፍ የተዘጋጁ የብድር መፍትሄዎችን ያቀርባል፡፡ ሥራዎን ለለማስፋፋት፣ አዳዲስ የሥራ እቃዎችን ለመግዛት ወይም የካፒታል ዕድረትዎን ለማሳደግ ባካችን ከአጭር እስከ ረጅም ጊዜ ብድሮችን በማቅረብ እድገትዎን ይደግፋል፡፡
የአጭር ጊዜ ብድር ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የፋይናንስ ክፍተቶችን ለመሸፈን ፈጣን የብድር አቅርቦት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ብድሮች እስከ 12 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ከሚመጡት የገንዘብ ፍሰቶች በፈጣን ክፍያ የሚጠናቀቁ በመሆናቸው ለድርጅቶች ተስማሚ ናቸው። እንደ ንግድዎ የገንዘብ ፍሰት ወይም ፍላጎቶች ላይ በመመስረት ክፍያ የመክፈያ የጊዜ ገደብ ሲደርስ ወይም በትክክለኛው በብድር መክፈያ ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ ይችላል፡፡
የዘመን ባንክ የመካከለኛ ጊዜ ብድር ለትርፍ ረዘም ያለ ጊዜ ለሚጠይቁ ኢንቨስትመንቶች የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሟላት የሚውል ብድር ነው፡፡ ይህ ብድር እስከ 5 ዓመት የክፍያ ጊዜ ያለው፣ ምቹ የብድር ክፍያዎችን በተጨማሪም እንደ ንግዱ የገቢ እና ወጪ ሂደት እና የፕሮጀክት ጊዜ ላይ የተመሰረተ የእፎይታ ጊዜ ያካትታል፡፡
የዘመን ባንክ የረጅም ጊዜ ብድር ትልቅ ካፒታል እና ረዘም ያለ የክፍያ ጊዜ ለሚያስፈልጋቸው ኢንቨስትመንቶች የሚውል ነው፡፡ ይህ ብድር ከአምስት ዓመት በላይ የክፍያ ጊዜ ያለው እና ለደንበኞች እንደ ንግዳቸው ሁኔታ የክፍያ ሁኔታዎች የሚመቻችላቸው ሲሆን ይህም ንግዳቸውን ለማሳደግ ይረዳቸዋል፡፡
የክሬዲት መስመር ለደንበኞች ቀጣይነት ያለው እስከ ተቀመጠለት ገደብ ድረስ ለየዕለት ተዕለት የሥራ ወጪዎቻቸው እና ላልተጠበቁ የገንዘብ ፍላጎታቸው ገንዘብ መበደር ያስችላቸዋል፡፡ ይህ ብድር ከደንበኞች የንግድ አካውንቶቻቸው ጋር የተጣመረ እና ገንዘብ በሚያሰፈልጋቸው ሰዓት ገንዘብ ማውጣት እና መክፈል ያስችላቸዋል፡፡
የሸቀጦች ብድር ለደንበኞች ለአጭር ጊዜ ለሸቀጣሸቀጦች ግዢ እና ሽያጭ የሚውል ደንበኞች የሸቀጣሸቀጦች ክምችታቸውን በገንዘብ እጥረት ምክንያት እንዳያጡ የሚውል ብድር ነው፡፡ ይህ ብድር በተለይ ወቅታዊ የግብይት ፍሰት ላላቸው ወይም ቶሎ ቶሎ የክምችት እንቅስቃሴ ላላቸው ንግዶች ጠቃሚ ነው ።
የዘመን ባንክ የቅድመ መላኪያ ኤክስፖርት ፋይናንስ የውጭ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች ለማምረት፣ለማሽግ እና ለማጓጓዝ የሚሰጥ ብድር ነው፡፡ ይህ ብድር በተረጋገጠ የኤክስፖርት ትዕዛዝ ወይም ክሬዲት ደብዳቤ ዋስትና ይሰጣል ።
ቅድመ ክፍያ ብድር በኤክስፖርት ሰነዶች ዋስትና ኤክስፖርተሮች ምርቶች ከላኩ በሆላ እና ክፍያ እስኪቀበሉ ድረስ ላለው ጊዜ የሚያገለግል ብድር ነው፡፡
ይህ ብድር አስመጪዎች በኢምፖርት ሰነዶች ዋስትና ለሚያስመጡዋቸው ዕቃዎች ክፍያ መፈጸም እንዲችሉ የሚያግዝ የአጭር ጊዜ ብድር ነው፡፡
በዘመን ባንክ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማነቃቃት ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚሆኑ የፋይናንስ መፍትሄዎችን በማቅረብ የበኩሉን ይወጣል፡፡ የዘርፉ ጥልቅ ዕውቀት፣ ቀልጣፋ የፋይናንስ መዋቅሮች እና በሙያው የተካኑ አማካሪዎች በተለያዩ መስኮች ያሉ የንግድ ድርጅቶች እንዲያድጉ እና እንዲበለፅጉ የሚያስፈልጋቸውን ካፒታል እና ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ።
ዘመን ባንክ የተለያዩ የባንክ ዋሰትና ሰነድ አግለግሎቶችን የሚያቀርብ ሲሆን ፡፡ ለጨረታ ማሰከበሪያ፣ ለአፈፃፀም፣ ለቅድመ ክፍያ፣ ለዱቤ አቅርቦት፣ እንዲሆም ለተለያዩ አለማዎች የሚውሉ የባንክ ዋሰትና ሰነድ አግለግሎቶችን ያቀረባል፡፡¨
ዘመን ባንክ ከሀገር ውስጥ እና/ወይም ከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ጋር በመተባበር በትልቅ መጠን የብድር ፍላጎት ላለቸው ማቅረብ የሚያስችል የተጋራ የፋይናንስ አገልግሎት ነው። ይህ አቀራረብ በብዙ የገንዘብ ፍላጎት ላቸው ፐሮጀክቶች ሃብት ማሰባሰብ እንዲከናወን ይረዳል፣ ለተበዳሪውም በአንድ የተጋራ የብድር መዋቅር ላይ ትልቅ የገንዘብ አቅረቦት እንዲያገኝ ያስችለዋል።
ዘመን ባንክ የጣምራ ፋይናንስ ሂደቶችን ማቅረብና ማከናወን ላይ በበለጠ ልምድ ያካበተ ሲሆን፣ የጋራ ብደር ስምምነቶችን (inter-creditor agreements) ፣ የዋስትና መገራት እና ወኪል የመሆን ስምምነቶች እና ተያያዥ የቅድመ ብደር ሂደቶችን የማከናወወን ከፍተኛ ተሞክሮ አለው።
Oct 3, 2025
Currency ConverterSEK
EUR
CAD
GBP
USD