የንግድ አገልግሎቶች

የድርጅት ብድር

ብድርዎ ቢያስፈልግዎ ዘመን ባንክ ለእርስዎ መፍትሄ አለው፡፡ የሥራ መጀመሪያ ካፒታል፣ የንብረት ፋይናንስ ወይም የፕሮጀክት ማስኬጃ ገንዘብ የሚያስፈልጎት ከሆነ ዘመን ባንክ ለእርስዎ የተዘጋጀና የተሟላ የገንዘብ አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ሁሉም የብድር ውሳኔዎች በባለሙያዎች የታገዘ ፈጣን ምላሽና ለእርስዎ የሚሆኑ መፍትሄዎችን የሚሰጡ ናቸው፡፡

የጊዜ ገደብ ብድር

ዘመን ባንክ የሥራዎን ዕድገትና የኢንቨስትመንት ግቦችዎን ለመደገፍ የተዘጋጁ የብድር መፍትሄዎችን ያቀርባል፡፡ ሥራዎን ለለማስፋፋት፣ አዳዲስ የሥራ እቃዎችን ለመግዛት ወይም የካፒታል ዕድረትዎን ለማሳደግ ባካችን ከአጭር እስከ ረጅም ጊዜ ብድሮችን በማቅረብ እድገትዎን ይደግፋል፡፡

ብድሮችና የክሬዲት አቅርቦት
የክሬዲት መስመር (የኦቨርድራፍ ፋሲሊቲ)

የክሬዲት መስመር ለደንበኞች ቀጣይነት ያለው እስከ ተቀመጠለት ገደብ ድረስ ለየዕለት ተዕለት  የሥራ ወጪዎቻቸው እና ላልተጠበቁ የገንዘብ ፍላጎታቸው ገንዘብ መበደር ያስችላቸዋል፡፡ ይህ ብድር ከደንበኞች የንግድ አካውንቶቻቸው ጋር የተጣመረ እና ገንዘብ በሚያሰፈልጋቸው ሰዓት ገንዘብ ማውጣት እና መክፈል ያስችላቸዋል፡፡

ለሸቀጦች የሚውል ብድርy

የሸቀጦች ብድር ለደንበኞች ለአጭር ጊዜ  ለሸቀጣሸቀጦች ግዢ እና ሽያጭ የሚውል  ደንበኞች  የሸቀጣሸቀጦች ክምችታቸውን  በገንዘብ እጥረት ምክንያት  እንዳያጡ የሚውል  ብድር ነው፡፡ ይህ ብድር በተለይ ወቅታዊ የግብይት ፍሰት  ላላቸው ወይም ቶሎ ቶሎ የክምችት እንቅስቃሴ ላላቸው ንግዶች ጠቃሚ ነው ።

የቅድመ መላኪያ ኤክስፖርት ፋይናንስ

የዘመን ባንክ የቅድመ መላኪያ ኤክስፖርት ፋይናንስ የውጭ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች ለማምረት፣ለማሽግ እና ለማጓጓዝ የሚሰጥ ብድር ነው፡፡ ይህ ብድር በተረጋገጠ የኤክስፖርት ትዕዛዝ ወይም ክሬዲት ደብዳቤ  ዋስትና ይሰጣል ።

የምናገለግላቸው ዘርፎች

በዘመን ባንክ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማነቃቃት ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚሆኑ የፋይናንስ መፍትሄዎችን በማቅረብ የበኩሉን ይወጣል፡፡ የዘርፉ ጥልቅ ዕውቀት፣ ቀልጣፋ የፋይናንስ መዋቅሮች እና በሙያው የተካኑ አማካሪዎች  በተለያዩ መስኮች ያሉ የንግድ ድርጅቶች እንዲያድጉ እና እንዲበለፅጉ የሚያስፈልጋቸውን ካፒታል እና ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ።

የንግድ አገልግሎቶች

ባሉበት ቦታ በመገኘት የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት

ይህ አገልግሎት ዘመን ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ላላቸው ደንበኞች ባሉበት ቦታ በመገኘት የባንክ አገልግሎቶቹን የሚያቀርብበት አሰራር ነው፡፡ ይህ ልዩ አገልግሎት በዘመን ባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች የሚያገኙዋቸውን አገልግሎቶች በቢሮዋቸውም ወይም በመኖርያ ቤታቸው በአካል በመገኘት በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ያስችላቸዋል፡፡

ይህን ልዩ አገልግሎት ደንበኞች የባንክ ፍላጎቶቻቸውን ባሉበት ሆነው በማግኘት የፋይናንስ እንቅስቃሴዎቻቸውን በቀላሉ እና በምቾት እንዲያከናውኑ ያስችለቸዋል፡፡

በደንበኞች የስራ ቦታ ላይ በመገኘት የደምወዝ ክፍያ አገልግሎት መስጠት

ዘመን ባንክ በደንበኞች የስራ ቦታ ላይ በመገኘት የደምወዝ ክፍያ አገልግሎትን ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ላላቸው ደንበኞች ያቀርባል፡፡ ይህ አገልግሎት በዘመን ባንክ በትላልቅ ኩባንያዎች ቅጥር ግቢ በመገኘት የሰራተኞችን ደመወዝ የሚከፍልበት አገልግሎት ነው፡፡ በዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት የባንክ አገልግሎቶቻቸውን እና የሰራተኞቻቸውን የደመወዝ ክፍያ ለዘመን ባንክ በመተው በራሳቸው የንግድ ወይም ሌሎች የድርጅቱ ዋናዋና እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ ብቻ  ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡

Reach us at