የንግድ አገልግሎቶች

የዘመን መደበኛ የቢዝነስ ሂሳቦች የድርጅቶችን መሰረታዊ የባንክ ፍላጎቶች በምቹና በተለያዩ አማራጮች ለማሟላት የተዘጋጀ የሂሳብ አይነት ነው።

ይህንን ሂሳብ ለመክፈት የመነሻ ተቀማጭ  ወለድ የማይታሰብበት ሲሆን በ5,000 ብር የሚከፈትና አማካኝ ወርሃዊ ዝቅተኛ ቀሪ ሂሳብ 25,000 ብር ነው፡፡

መደበኛ የቢዝነስ ሂሳብ ባለቤቶች ያልተገደበ ቼክ የጽሑፍ መብቶችንና የኢንተርኔት ባንኪንግ፣ የኤቲኤም አገልግሎቶች፣ የሞባይል ባንኪንግና ሌሎችንም ጨምሮ በሁሉም የአገልግሎት አማራጮች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ይህም ምቹና እንከን የለሽ የግብይት ሂደቶችን በማንኛውም ጊዜና ቦታ መፈፀም እንዲችሉ ይረዳቸዋል።

የእኛ የቢዝነስ ቁጠባና የቢዝነስ አድቫንቴጅ ሂሳቦች ለደንበኞች ተለዋዋጭነት ያላቸው መፍትሄዎች የሚያቀርቡ ሂሳቦች ናቸው።

ይህ አካውንት 5,000 ብር የመጀመሪያ ተቀማጭ የሚያስፈልገው ሲሆን በአማካይ በየቀኑ 100,000 ብር በሂሳቡ ሊኖረው ያስፈልጋል። የሚፈለገውን ቀሪ ሂሳብ ለማሟላት ሂሳቡ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የ10 ቀናት የእፎይታ ጊዜ ይሰጠዋል። ሂሳቡ በወርሃዊ ዝቅተኛ ቀሪ ሂሳብ ላይ የሚሰላው በዓመት 7% የወለድ መጠን ያገኛል።

በዚህ ሂሳብ ድርጅቶች ከቁጠባና ከቼክ ሂሳቦች ጥምር ጥቅሞች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪም ወለድ እንዲያገኙ በመፍቀድ እንዲሁም የቼኮችና ሌሎች ግብይቶችን በሚፈፅሙ ጊዜ ፈጣንና ምቹ አገልግሎቶችን ያገኛሉ። ለደንበኞቻችን ለተሻሻለ የሥራ ቅልጥፍና የበኩሉን የሚያበረክተውን ኦምኒ ቻናል የባንክ አማራጮችና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች እንዲጠቀሙም ያስችላል።

የዘመን ባንክ ኦቨርድራፍት ፕሮቴክሽን የቼክና የቁጠባ ሂሳቦችን በጋራ ለሚጠቀሙ ደንበኞች የአእምሮ ሰላም ይሰጣል።

የቼክና የቁጠባ ሂሳብ ያለው ደንበኛ የቁጠባ ሂሳቡን ለቼኪንግ ሂሳቡ እንደ ኦቨርድራፍት ፕሮቴክሽን መጠቀም ይችላል። አንድ ደንበኛ በቼኪንግ አካውንቱ ላይ ቼክ ከፃፈ በኋላ በቂ ገንዘብ ከሌለው ከቁጠባ ሂሳቡ ከሚገኘው ገንዘብ በመጠቀም ልዩነቱን ለመሙላት ሊገለገልበት ይችላል። ለዚህም አገልግሎት ብር 20 ይከፍላል፡፡

ዘመን ባንክ ሥራ መቋረጥ እንደሌለበትና በሚያስፈልግዎት ጊዜ የባንክ አገልግሎቶች ማግኘት እንደሚገባዎ ያምናል፡፡ ለዚያም ነው ፍላጎትዎን ለማሟላት ደህንነታቸው የተጠበቀ የተለያዩ የባንክ መፍትሄዎችን የምናቀርብላችሁ።

ፋይናንስዎን በሥራ ሰዓትም ሆነ ከሥራ ሰዓት ውጪ ለማስተዳደር ይረዳዎ ዘንድ የኦምኒ ቻናል ማለትም የኢንተርኔት ባንኪንግ፣ የሞባይል ባንክና ባሉበት ቦታ ተገኝተን የባንካችንን አገልግሎት መስጠት እንዲሁም ፖስና ኤቲም አገልግሎቶችን በማንኛውም ጊዜና ቦታ መጠቀም ይችላሉ።

በዘመን ባንክ በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ምቹ፣ ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎትን ያገኛሉ፡፡

ባሉበት ቦታ በመገኘት የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት

ይህ አገልግሎት ዘመን ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ላላቸው ደንበኞች ባሉበት ቦታ በመገኘት የባንክ አገልግሎቶቹን የሚያቀርብበት አሰራር ነው፡፡ ይህ ልዩ አገልግሎት በዘመን ባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች የሚያገኙዋቸውን አገልግሎቶች በቢሮዋቸውም ወይም በመኖርያ ቤታቸው በአካል በመገኘት በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ያስችላቸዋል፡፡

ይህን ልዩ አገልግሎት ደንበኞች የባንክ ፍላጎቶቻቸውን ባሉበት ሆነው በማግኘት የፋይናንስ እንቅስቃሴዎቻቸውን በቀላሉ እና በምቾት እንዲያከናውኑ ያስችለቸዋል፡፡

በደንበኞች የስራ ቦታ ላይ በመገኘት የደምወዝ ክፍያ አገልግሎት መስጠት

ዘመን ባንክ በደንበኞች የስራ ቦታ ላይ በመገኘት የደምወዝ ክፍያ አገልግሎትን ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ላላቸው ደንበኞች ያቀርባል፡፡ ይህ አገልግሎት በዘመን ባንክ በትላልቅ ኩባንያዎች ቅጥር ግቢ በመገኘት የሰራተኞችን ደመወዝ የሚከፍልበት አገልግሎት ነው፡፡ በዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት የባንክ አገልግሎቶቻቸውን እና የሰራተኞቻቸውን የደመወዝ ክፍያ ለዘመን ባንክ በመተው በራሳቸው የንግድ ወይም ሌሎች የድርጅቱ ዋናዋና እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ ብቻ  ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡