ቅድመ-ገፅ » የክፍያ ካርድ ህትመት አገልግሎት
ዘመን ባንክ የፒ.ሲ.አይ ዲ.ኤስ.ኤስ መስፈርቶችን ያሟላ የክፍያ ካርዶድ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥ ቢሮ በመገንባት የተለያዩ አይነት የክፍያ ካርዶችን በማተም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ በራሳቸው ቢሮ የክፍያ ካርድ ህትመት ከሚሰጡ ጥቂት ባንኮች አንዱ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የፒ.ሲ.አይ ዲ.ኤስ.ኤስ የደህንነት ደረጃዎችን እና መመዘኛዎችን በመሟላት አለማቀፍ ተቀባይነት ያለው የማረጋገጫ ሰርተፍኬት በማግኘት በኢትዮጵያ ቀዳሚው ባንክ ነው፡፡
ባንካችን በክፍያ ካርድ ህትመት አገልግሎቱ ስር የፕላቲኒየም ቅድመ ክፍያ የጉዞ ማስተር ካርድን ጨምሮ የተለያዩ የክፍያ ካርድ ህትመት አገልግሎቶችን የይሰጣል፡፡ ይህም ዘመን ባንክን ዓለም አቀፍ የጉዞ ቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድን በኢትዮጵያ ገበያ በማስተዋወቅ ቀዳሚ ባንክ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ ባንካችን የተለያዩ አይነት የዴቢት ካርዶችን ፣ የቅድመ ክፍያ የሀገር ውስጥ ካርዶችን እና የስጦታ ካርዶችን በማቅረብ የደንበኞችን ፍላጎት በማሟላት ላይ ይገኛል፡፡
የዘመን ዴቢት ካርዶችን መጠቀም 24 ሰዓት ሙሉ በሂሳብዎ እንዲገለገሉ ያደርጋል። የዘመን ንክኪ አልባ ዴቢት ካርድ ከኤቲኤም ካርድ በላይ ነው፤ ይህም በ ፖስ ማሽኖች ላይ ፣ በኦንላይን ግብይት እና በኤ.ቲ.ኤም ላይ ግብይቶችን ለመፈፀም ያስችልዎታል።
ዘመን ባንክ ከሚያቀርባቸው የተለየዩ አይነት የዴቢት ክፍያ ካርዶች ውስጥ ቤዚክ ዴቢት ካርድ ፣ ፕሪስቲጅ ዴቢት ካርድ እንዲሁም የዚ-ክለብ ዴቢት ካርድ ተጠቃሾች ናቸው።
ዘመናዊ የንግድ ድርጅቶችን ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጀው የደመወዝ ካርዳችን የሠራተኞችን ደመወዝ በካርዳቸው በኩል እንዲከፈላቸው በማስቻል አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል ። አመቺና ተደራሽ የክፍያ አማራጭ በመስጠት የደመወዝ ክፍያ ሂደትዎን ማቀላጠፍ ይቻላል ።
በዘመን ባንክ የቅድመ ክፍያ ካርድ አማካኝነት በየቀኑ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጡ ሙሉ ቁጥጥር ማድረግ ይችላሉ። በቅድመ ክፍያ ካርድ ላይ የሚሞሉት የገንዘብ መጠን ሊከፈል የሚችል ከፍተኛው መጠን ነው።
የቅድመ ክፍያ ካርድዎን ገንዘብ መሙላት ሲፈልጉ የዘመን ባንክ ቅርንጫፎችን መጎብኘት ሳይጠበቅብዎ የዘመን ባንክን የሞባይል ወይም የኢንተርኔት ባንኪንግ አማራጮችን በመጠቀም ለጉዞና ለግብይት የሚያስፈልግዎትን ገንዘብ በቅድመ ክፍያ ካርድዎ ላይ ራስዎ መሙላት ይችላሉ፡፡
የዘመን ባንክ ቅድመ ክፍያ ካርድ ወጪንና በጀትን በተገቢው መንገድ ለመቆጣጠር ያስችላል። በዚህም ካርድዎ ላይ የሚፈልጉትን ያህል ገንዘብ በመሙላት እና የተሞላውን ገንዘብ ብቻ እንዲጠቀሙ በማድረግ ከእቅድ በላይ ያለን ወጪ ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
ለዓመት በዓል፣ ለልደት፣ ለክብረ በዓልና ለመሳሰሉት ዝግጅቶች ጥሩ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ? የአቅራቢያዎ የሚገኙ የባንካችንን ቅርንጫፎች በማነጋገር የስጦታ ካርድ አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዘመን ስጦታ ካርድ በኮርፖሬት ደረጃ ለሠራተኞች፣ ለበዓላትና ለአጋሮች ወዘተ ስጦታ ለመስጠት ሊውል ይችላል፡፡
የስጦታ ካርዶቻችን በሁሉም የዘመንና የሌሎች ባንኮች ፖስ እና ኤቲኤም ማሽኖች ተቀባይነት ስላላቸው ፣ ገንዘብ ወጪ ለማድረግና ክፍያ ለመፈፀም ምቹ እና ተመራጭ ነው፡፡
ዘመን ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የቅድመ ክፍያ ንክኪ አልባ አለማቀር የጉዞ ካርድ ለኢትዮጵያውያን ተጓዦች በዩሮ እና በዶላር ምንዛሪ አማራጮች በማቅረብ በኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ ባንክ ነው፡፡ በዚህም ኢትዮጵያውያን ተጓዦች ጥሬ ገንዘብ ይዘው የሚያደርጉትን አለማቀፍ ጉዞ በማዘመን ክፍያዎቻቸውን በቀላሉ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲፈፅሙ ያስችላል፡፡
ዘመን ባንክ በሀገሪቱ ውስጥ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የባንክ አሰራሮችን በማስተዋወቅ የሚታወቅ ባንክ ሲሆን የህንን ንክኪ አልባ አለማቀፍ የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርድ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆነን በማቅረባችን እና ለደንበኞቻችን ምቾት እና ደህንነትን በመፍጠራችን ኩራት ይሰማናል፡፡
ያለካርድ ገንዘብ ማውጣት አገልግሎታችን አማካኝነት ካርድ ሳይዙ በዘመን ባንክ ኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ ። ካርድ አልባው መፍትሄ ካርድዎን በኪስዎ ፤ በቤትዎ ወይም ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ የሞባይል ስልክዎን በመጠቀም ብቻ ገንዘብ ከኤ.ቲ.ኤም እንዲያወጡ ያስችልዎታል።
የዲጂታል ባንኪንግ አቅርቦታችን በሞባይልና በበይነመረብ ባንኪንግ የላቀ አገልግሎት የምንሰጥበት ነው፡፡ ደንበኞች በቀላሉ እንዲጠቀሙና የባንክ አገልግሎትን ባሉበት ሆነው በራሳቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
Oct 3, 2025
Currency ConverterSEK
EUR
CAD
GBP
USD