ዘመን ባንክ የደንበኞችን የምስጋና እና እውቅና ቀን ረዥም ግዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞችን እና አጋሮቹን በመሸለም እና እውቅና በመስጠት አከበረ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 07፣ 2017 ዓ.ም ዘመን ባንክ የደንበኞችን የምስጋና እና እውቅና ቀን ረዥም ጊዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞቹን እና አጋሮቹን በሸራተን ሆቴል በመሸለም እና እውቅና በመስጠት አከበረ፡፡በዕለቱም ከ250 በላይ ለሆኑ አብረውት ሲሰሩ ለቆዩ ውድ ደንበኞች እና አጋሮች ማለትም በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአየር ትራንሰፖርት፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ለተሰማሩ እንዲሁም አብረውት ለሚሰሩ ዓለም-አቀፍ […]

ዘመን ባንክ የኢትዮጲያ ኔዘርላንድስ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) አባል በመሆን አብሮ ለመስራት የሚያስችላለውን ስምምነት ነሐሴ 22 ቀን 2024 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ዘመን ባንክ የኢትዮጵያ – ኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) ስር ካሉ ዘርፈ ብዙ ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖረውን አጋርነትን ከማጠናከሩም በላይ ባንኩ ዘላቂ የባንክ እገዛ እና አጋርነትን ከሚፈልጉ መሰል ተቋማት ጋር አብሮ የመስራት እቅዱን ለማሳካት ያሰችለዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ማህበሩ እና አባላቱ የዘመን ባንክን ዘመናዊ እና ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ።