ዘመን ባንክ በአረንጓዴ ፋይናንስ ፕሮግራም ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

በሀገራችን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ጋር ተያይዞ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በተከናወነው መርሃግብር ላይ ዘመን ባንክን በመወከል አቶ ተዋህዶ ታፈሰ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር ስምምነቱን ተፈራርመዋል። በዚህ አጋርነት፤ ዘመን ባንክ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን የመገምገም፣ በፋይናንሱ ዘርፍ ዘላቂ አጋርነትን ለማስመዝገብና ዓላማውን ለማሳካት የሚያግዙ ብድሮችን በማመቻቸት የበኩሉን ይወጣል፡፡በዝግጅቱ ወቅት አቶ ተዋህዶ እንደገለፁት ይህ […]

ዘመንባንክ “የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የኢትዮጵያ የባንክዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ” በሚልርዕሰ ጉዳይ ላይ የፓናል ውይይት አካሄደ

የአገራችን የባንክ ሥራ የወደፊት አቅጣጫ ስኬታማ እንዲሆን ዘላቂነት ያለው፣ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያገለግል የፋይናንስ ሥርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ እንዬ ቢምር፣ የዘመን ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አሳሰቡ፡፡ ዘመን ባንክ “የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ሰብሳቢዋ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ባንኩ ገንቢ፣ ቀዳሚና አመራሩ ጠንካራ […]