የዘመን ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የምልመላ እና የምርጫ አፈፃፀም መመሪያ የመመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻል
1. የዘመን ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የምልመላ እና የምርጫ አፈፃፀም መመሪያ – መመሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ 2. የዘመን ባንክ አ.ማ. የመመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻል ሀሳቦችን በዚህ ማስፈንጠሪያ ያውርዱ
የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ
የዘመን ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ለተከበራችሁ የዘመን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣367(1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ የተሻሻለው የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 12.1፣12.5 ፣13 እና አንቀጽ 14.1 መሠረት የዘመን ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 17ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 1. ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና […]
ዘመን ባንክ በአረንጓዴ ፋይናንስ ፕሮግራም ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

በሀገራችን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ጋር ተያይዞ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በተከናወነው መርሃግብር ላይ ዘመን ባንክን በመወከል አቶ ተዋህዶ ታፈሰ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር ስምምነቱን ተፈራርመዋል። በዚህ አጋርነት፤ ዘመን ባንክ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን የመገምገም፣ በፋይናንሱ ዘርፍ ዘላቂ አጋርነትን ለማስመዝገብና ዓላማውን ለማሳካት የሚያግዙ ብድሮችን በማመቻቸት የበኩሉን ይወጣል፡፡በዝግጅቱ ወቅት አቶ ተዋህዶ እንደገለፁት ይህ […]
ዘመንባንክ “የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የኢትዮጵያ የባንክዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ” በሚልርዕሰ ጉዳይ ላይ የፓናል ውይይት አካሄደ

የአገራችን የባንክ ሥራ የወደፊት አቅጣጫ ስኬታማ እንዲሆን ዘላቂነት ያለው፣ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያገለግል የፋይናንስ ሥርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ እንዬ ቢምር፣ የዘመን ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አሳሰቡ፡፡ ዘመን ባንክ “የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ሰብሳቢዋ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ባንኩ ገንቢ፣ ቀዳሚና አመራሩ ጠንካራ […]
ዘመን ባንክ የደንበኞችን የምስጋና እና እውቅና ቀን ረዥም ግዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞችን እና አጋሮቹን በመሸለም እና እውቅና በመስጠት አከበረ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 07፣ 2017 ዓ.ም ዘመን ባንክ የደንበኞችን የምስጋና እና እውቅና ቀን ረዥም ጊዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞቹን እና አጋሮቹን በሸራተን ሆቴል በመሸለም እና እውቅና በመስጠት አከበረ፡፡በዕለቱም ከ250 በላይ ለሆኑ አብረውት ሲሰሩ ለቆዩ ውድ ደንበኞች እና አጋሮች ማለትም በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአየር ትራንሰፖርት፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ለተሰማሩ እንዲሁም አብረውት ለሚሰሩ ዓለም-አቀፍ […]
ዘመን ባንክ የኢትዮጲያ ኔዘርላንድስ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) አባል በመሆን አብሮ ለመስራት የሚያስችላለውን ስምምነት ነሐሴ 22 ቀን 2024 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ዘመን ባንክ የኢትዮጵያ – ኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) ስር ካሉ ዘርፈ ብዙ ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖረውን አጋርነትን ከማጠናከሩም በላይ ባንኩ ዘላቂ የባንክ እገዛ እና አጋርነትን ከሚፈልጉ መሰል ተቋማት ጋር አብሮ የመስራት እቅዱን ለማሳካት ያሰችለዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ማህበሩ እና አባላቱ የዘመን ባንክን ዘመናዊ እና ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 – ትግበራ
ለክቡራን ደንበኞቻችን፤ ባንኮች ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሰበስቡ መንግሥት በቅርቡ ባወጣው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 ላይ ደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት ዘመን ባንክ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ክፍያ ላይ ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚታከልበት መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ዘመን ባንክ አ.ማየላቀ አገልግሎት ማዕከል!
ዘመን ባንክና የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ፋይናንስ ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ተፈራረሙ

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዘመን ባንክን አዲሱ የአለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ፕሮግራም Global Trade Finance Program (GTFP) አባል አድርጎ በመቀበል ባንኩ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት የፋይናንስ ዋስትና እንደሚያቀርብ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡ በዚህ ስምምነት የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የዘመን ባንክን የትሬድ ፋይናንስ (የወጪና ገቢ ንግድ ገንዘብ አቅርቦት) እንቅስቃሴ ለማጠናከርና በኢትዮጵያ […]
ዘመን ባንክ እና የኢትዮጵያ-ኔዘርላንድስ ቢዝነስ ማህበር የትብብር ስምምነት አደረጉ፡፡

ዘመን ባንክ የኢትዮጲያ ኔዘርላንድስ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) አባል በመሆን አብሮ ለመስራት የሚያስችላለውን ስምምነት ነሐሴ 22 ቀን 2024 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱ ዘመን ባንክ የኢትዮጵያ – ኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) ስር ካሉ ዘርፈ ብዙ ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖረውን አጋርነትን ከማጠናከሩም በላይ ባንኩ ዘላቂ የባንክ እገዛ እና አጋርነትን ከሚፈልጉ መሰል ተቋማት ጋር አብሮ የመስራት […]