የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት

ለማንኛውም የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ዘመን ባንክ የእርስዎ ምርጫ ነው። የተለያዩ የውጭ ሃገራት ምንዛሪ አገልግሎቶችን በነዚህ አማራጮች ማግኘት ይችላሉ፡፡

የውጪ ምንዛሪ ሂሳቦች ለውጭ ሀገር ድርጅቶች

ይህ የቁጠባ ሂሳብ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ  የተዘጋጀ ሲሆን ሂሳቡን ለመክፈት የተቀመጡትን መስፈርቶች ለሚያሟሉ በኤምባሲዎች፣ በውጭ ንግድ ማህበረሰብ ፣ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች (በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ምንዛሪ) ለሚከፈላቸው የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ሂሳብ ወለድ የማይታሰብለት እና ቁጠባዎች በውጪ ሃገር ገንዘብ የሚቀመጥበት ነው ፡፡ተጨማሪ ገቢ ገንዘቦች በጉምሩክ ከተገለጸ፣  ከጉዞ ወጪ የሚመለስ ገንዘብ ከሆነ ወይም ነዋሪ ካልሆኑ የውጭ ምንዛሪ እና ከሌሎች በዲያስፖራ ቁጠባ ሒሳቦች  የሚተላለፉ እና ከየውጭ አገር ዜጎች  ሂሳብ የተወሰዱ ቼኮች ተጨማሪ ገንዘቦችን በውጭ ምንዛሪ ማስገባት ይችላሉ። ክፍያዎችም በኢትዪጵያ ብር መፈፀም ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜግነት ለሌላቸው እና የኢትዮጵያ ዜግነት ለሌላቸው የተዘጋጁ የውጪ ምንዛሪ ሂሳቦች - እነዚህ የቁጠባ ሂሳቦች ሂሳቡን ለመክፈት የተቀመጡትን መስፈርቶች ለሚያሟሉ

  • የኢትዮጵያ ዜግነት ለሌላቸው ከአንድ አመት በላይ ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚሰሩ 

ትውልደ ኢትዮጵያውያን

የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው ግለሰቦች ፣ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና በአለም አቀፍ ድርጅቶችየሚሰሩ 

እነዚህ ሂሳቦች ቁጠባዎች በውጪ ሃገር ገንዘብ የሚቀመጥበት ሲሆን በጉምሩክ ከተገለጸ፣  ከጉዞ ወጪ የሚመለስ ገንዘብ ከሆነ ወይም ነዋሪ ካልሆኑ የውጭ ምንዛሪ እና ከሌሎች በዲያስፖራ ቁጠባ ሒሳቦች  የሚተላለፉ እና ከየውጭ አገር ዜጎች  ሂሳብ የተወሰዱ ቼኮች ተጨማሪ ገንዘቦችን በውጭ ምንዛሪ ማስገባት ይችላሉ።

ሪቴንሽን ሂሳቦች

በብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ኖቶችን እና የክሬዲት ካርድ/ዴቢት ካርድ/ቅድመ ክፍያ ካርድ እና ክፍያ ለመፈጸም  ፈቃድ የተሰጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላኪ፣ነጋዴዎች እና/ወይም ድርጅቶች ይህንን አካውንት የውጪ ምንዛሪያቸውን ይዘው ለመቆየት መክፈት ይችላሉ፡፡ ይህ አካውንት USD EUR GBP ወይም ሌላ በብሄራዊ ባንክ  ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ሊከፈት ይችላል።