ዘመን ባንክ አ.ማ. በ18ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ ባንኩን ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚመሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ያካሂዳል፡፡
ስለሆነም ባንኩን በገለልተኛ ዳይሬክተርነት ማገልገል የምትፈልጉና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ከታች የተቀመጠውን አድራሻ በመጠቀም እንድታመለክቱ የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ገለልተኛ የዳይሬክተሮች ቦርድ (Independent Directors) አባል ሆኖ ለመመረጥ ዕጩዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1.በባንኪንግ፣ በፋይናንስ፣ በስጋት አስተዳደር፣ በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣በኢኮኖሚክስ፣ በህግ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በኦዲት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም ተመሳሳይ የሙያ ዘርፎች ቢያንስ በማስተርስ ዲግሪ የተመረቀና ቢያንስ የአስር ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፤
2.ከባንክ ሥራ ጋር ተዛማጅ የሆኑ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን የወሰደ፤
3.በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እምነት በማጉደል፣ በማጭበርበር፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ወንጀሎች ተከሶ በፍ/ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣
4.ዳይሬክተር ወይም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ባለቤት በሆነበት ድርጅት መክሰር ሂደት ያላስጀመረ ወይም መክሰሩ ያልተወሰነበት፣ ንብረት ያልተወረሰበት፣ ንብረቱ በመክሰር ውሳኔ መሠረት እንዲተዳደር ያልተደረገበት ወይም የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ ለእዳ ማስመለሻነት ያልተሸጠበት፤
5.በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣ ግብር ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፤
6.ግለሰቡ በራሱ ወይም በሚስቱ ወይም በልጁ የባንኩ ባለአክሲዮን ያልሆነ፣ ከባንኩ ጋር ሙያዊ ሆነ የንግድ ሥራ ግንኙነት የሌለው፤
7.ግለሰቡ ራሱ ወይም ሚስቱ ወይም ልጁ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያልሆነ፣ ወይም በባንኩ ውስጥ ከፍተኛ ሥራ አመራር ደረጃ ላይ የማይገኝ፣ በባንኩ የዕለት ተዕለት ሥራ ላይ ተሳታፊ ያልሆነ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከባንኩ ጋር የሥራ፣ የሙያዊ ወይም የንግድ ግንኙነት የሌለው፤
8.ከባንኩ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ክርክር የሌለው፤
9.የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም እሱ የሚመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልገባበት፤
10.ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ መመሪያዎች ላይ የተገለጹት ሌሎች መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆን አለበት፤
11.በወንድ ፆታ የተገለፀው ለሴት ፆታም ያገለግላል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎች
አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚከተለውን አድራሻ በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ፡፡ https://applybod.zemenbank.com
የመጀመሪያውን ዙር ማጣሪያ ላለፉ ተወዳዳሪዎች የቃለ መጠይቅ የፈተና ቀን በባንኩ ድረ ገጽ እና አመልካቾች ባስቀመጡት አድራሻ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
በአካል የሚመጡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
በማመልከቱ ሂደት የቴክኒክ እርዳታ ካስፈለገዎት በሚከተለው አድራሻ በመጠቀም እርዳታ ማግኘት ይችላሉ፡፡
| Helina Bikes | Helina.Bikes@zemenbank.com | +251963327539 |
| Hawi Tena | Hawi.Tena@zemenbank.com | +251984579558 |




