ዘመን ባንክ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ አተረፈ አጠቃላይ የሀብቱ መጠን 116 ቢሊየን ብር ደረሰ

ዘመን ባንክ በ2017/2018 (እ.አ.አ 2025/26) በጀት ዓመት 10.2 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ የሀብቱ መጠን 116 ቢሊየን ብር ደርሷል፡፡ የባንኩ ዓመታዊ የማኔጅመንት ስብሰባ ከሐምሌ 17 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደበት ወቅት ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ባደረጉት ንግግር፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የላቀ ውጤት መገኘቱን ገልጸው፤ ለዚህ ስኬት ለባንኩ የማኔጅመንት […]