ዘመን ባንክ የሴቶች በዲፕሎማሲ ኔትወርክ በኢትዮጵያ (WIDEN) አጋር በመሆን ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ዓለም አቀፍ የሴቶች የዲፕሎማሲ ቀንን በጋራ አክብሯል።

የሴቶች በዲፕሎማሲ ኔትወርክ በኢትዮጵያ (WIDEN) ከዓለም አቀፍ የሥርዓተ-ፆታ ሻምፒዮናዎች ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ አምባሳደሮችን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችን፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መሪዎችን በጋራ አሰባስቧል፡፡ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማሳደግና የሴቶችን የአመራር ብቃት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ የተቃኘ እንዲሆን የሚረዳ ነው።
በዝግጅቱ ላይ ፍትሃዊ የአመራር ሥርዓትን አስፈላጊነት እና በአካታች አመራር ብቃት ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ንግግሮች ቀርበዋል። ዝግጅቱ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማጎልበት እንዲሁም በአመራርና በውሳኔ ሰጪነት ሚናዎች የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል “Gender Parity Pledge” የተሰኘ አዲስ እንቅስቃሴም ያካተተ ነበር።

ዘመን ባንክ ማኃበረሰብን በማብቃትና ሁሉን አቀፍ እድገትን በማጎልበት የሚያምን ባንክ በመሆኑ የሴቶችን አመራር፣ እኩልነትና ዘላቂ ማኃበራዊ እድገትን የሚያበረታታውን ይህን ዝግጅት ስፖንሰር በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል።




