‘’ የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪን መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላል’’ አቶ ሚካኤል ፀጋዬ

የዘመን ባንክ ቺፍ ሆልሴል ባንኪን ኦፊሰር አቶ ሚካኤል ፀጋዬ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪን መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፁ፡፡ አቶ ሚካኤል ይህን የገለፁት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (አይኤቲኤ) የፎከስ አፍሪካ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ አቶ ሚካኤል በኢትዮጵያ እየተሻሻለ የመጣውን የፋይናንስ ሁኔታና በቀጥታ ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተመለከተ ማብራሪያ ያቀረቡ […]
ዘመን ባንክ ለዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር አጋርነቱን አሳየ

ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) በአዲስ አበባ ባዘጋጀውና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የተወከሉ ተሳታፊዎች ለተገኙበት ኮንፈረንስ ዘመን ባንክ ግንባር ቀደም አጋርነትን አሳየ፡፡ የአፍሪካን አቪዬሽን ደህንነት፣ ተደራሽነትና ኦፕሬሽናል ብቃት ላይ በማተኮር የሚካሄደው ስብሰባ በስካይ ላይት ሆቴል ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በተከፈተበት ወቅት ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፣ አቶ አስራት […]
ዘመን ባንክና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚውል 40 ሚሊዮን ዩሮ ለማቅረብ ተስማሙ

ዘመን ባንክና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ – ግሎባል በአውሮፓ ህብረትና የኢትዮጵያ ቢዝነስ ፎረም ወቅት በግብርና ለተሰማሩ ተቋማት የሚውል 40 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈራርመዋል። በስምምነቱ መሰረት የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ 20 ሚሊዮን ዩሮ ለዘመን ባንክ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ዘመን ባንክ በበኩሉ ተመሳሳይ መጠን ያለው ገንዘብ በኢትዮጵያ ብር ለተጠቃሚዎች ያቀርባል። ይህም ኢንቨስትመንት ባንኩ በኢትዮጵያ ውስጥ ለንግድ ባንክ በቀጥታ የሰጠው የመጀመሪያው […]
ዘመን ባንክ ከአስፓየር ማይክሮ ፋይናንስ ጋር የስትራቴጂካዊ አጋርነት ፊርማ ተፈራረመ

ዘመን ባንክ እና አስፓየር ማይክሮ ፋይናንስ (በምስረታ ላይ) በፋይናንስ አካታችነት፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና በኢኮኖሚ ልማት ዙሪያ ትብብርን ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ ። የስትራቴጂካዊ አጋርነቱ ዓላማ የባንክና የገንዘብ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ማስፋት ፣ ዘመናዊ የፋይናንስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና በዲጂታል ፋይናንስ ዙሪያ በጋራ ለመስራትና ተቋማዊ አቅምን ማጎልበት ነው ። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አቶ አዲስ ወልደጨርቆስ የዘመን ባንክ የብድር ቺፍ ኦፊሰር […]
ዘመን ባንክ የ85 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ፋሲሊቲ አገኘ!

ዘመን ባንክ አጋሮቹ ከሆኑት ከአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) እና ከትሬድና ዴቨሎፕመንት ባንክ (TDB) በድምሩ 85 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ፋሲሊቲ በተሳካ ሁኔታ ማግኘቱን ስንገልጽ በደስታ ነው።ይህ ፋሲሊቲ ዘመን ባንክ የገቢና ወጪ ንግድ ልውውጦችን በተሻለ መልኩ ለመደገፍ፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች የውጭ ምንዛሪ ተደራሽነትን ለማሻሻልና በተለዋዋጭ ገበያ ውስጥ ባንኩ ለደንበኞች ፍላጎት ቀልጣፋ ምላሽ መስጠት እንዲችል ያግዘዋል፡፡ዘመን […]
ዘመን ባንክ በአረንጓዴ ፋይናንስ ፕሮግራም ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

በሀገራችን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ጋር ተያይዞ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በተከናወነው መርሃግብር ላይ ዘመን ባንክን በመወከል አቶ ተዋህዶ ታፈሰ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር ስምምነቱን ተፈራርመዋል። በዚህ አጋርነት፤ ዘመን ባንክ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን የመገምገም፣ በፋይናንሱ ዘርፍ ዘላቂ አጋርነትን ለማስመዝገብና ዓላማውን ለማሳካት የሚያግዙ ብድሮችን በማመቻቸት የበኩሉን ይወጣል፡፡በዝግጅቱ ወቅት አቶ ተዋህዶ እንደገለፁት ይህ […]
ዘመንባንክ “የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የኢትዮጵያ የባንክዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ” በሚልርዕሰ ጉዳይ ላይ የፓናል ውይይት አካሄደ

የአገራችን የባንክ ሥራ የወደፊት አቅጣጫ ስኬታማ እንዲሆን ዘላቂነት ያለው፣ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያገለግል የፋይናንስ ሥርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ እንዬ ቢምር፣ የዘመን ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አሳሰቡ፡፡ ዘመን ባንክ “የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ሰብሳቢዋ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ባንኩ ገንቢ፣ ቀዳሚና አመራሩ ጠንካራ […]
ዘመን ባንክ የደንበኞችን የምስጋና እና እውቅና ቀን ረዥም ግዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞችን እና አጋሮቹን በመሸለም እና እውቅና በመስጠት አከበረ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 07፣ 2017 ዓ.ም ዘመን ባንክ የደንበኞችን የምስጋና እና እውቅና ቀን ረዥም ጊዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞቹን እና አጋሮቹን በሸራተን ሆቴል በመሸለም እና እውቅና በመስጠት አከበረ፡፡በዕለቱም ከ250 በላይ ለሆኑ አብረውት ሲሰሩ ለቆዩ ውድ ደንበኞች እና አጋሮች ማለትም በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአየር ትራንሰፖርት፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ለተሰማሩ እንዲሁም አብረውት ለሚሰሩ ዓለም-አቀፍ […]
ዘመን ባንክ የኢትዮጲያ ኔዘርላንድስ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) አባል በመሆን አብሮ ለመስራት የሚያስችላለውን ስምምነት ነሐሴ 22 ቀን 2024 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ዘመን ባንክ የኢትዮጵያ – ኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) ስር ካሉ ዘርፈ ብዙ ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖረውን አጋርነትን ከማጠናከሩም በላይ ባንኩ ዘላቂ የባንክ እገዛ እና አጋርነትን ከሚፈልጉ መሰል ተቋማት ጋር አብሮ የመስራት እቅዱን ለማሳካት ያሰችለዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ማህበሩ እና አባላቱ የዘመን ባንክን ዘመናዊ እና ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ዘመን ባንክና የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ፋይናንስ ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ተፈራረሙ

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዘመን ባንክን አዲሱ የአለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ፕሮግራም Global Trade Finance Program (GTFP) አባል አድርጎ በመቀበል ባንኩ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት የፋይናንስ ዋስትና እንደሚያቀርብ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡ በዚህ ስምምነት የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የዘመን ባንክን የትሬድ ፋይናንስ (የወጪና ገቢ ንግድ ገንዘብ አቅርቦት) እንቅስቃሴ ለማጠናከርና በኢትዮጵያ […]