የዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበርየባለአክሲዮኖች 18ኛ መደበኛ እና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

የተከበራችሁ የዘመን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ህግ አንቀፅ 366/1፣ 367/1 እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀፅ 12.1፣ 12.5፣ 13 እና 14.1 መሰረት የዘመን ባንክ አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች 18ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሲኤምሲ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው አዲስ […]

ዘመን ባንክ የመረጃ ደህንነት አስተዳደር ሥርዓት የISO/IEC 27001:2022 ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ አገኘ

ዘመን ባንክ የመረጃ ደህንነት አስተዳደር ሥርዓት (Information Security Management System) የሚሰጠውንነና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውን የISO/IEC 27001:2022 መስፈርት በማሟላት የማረጋገጫ ሰርቲፊኬት አገኘ። ይህ ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ ባንኩ የደንበኞቹን መረጃ አስተማማኝነት ለማረጋገጥ፣ ለሥራው ወሳኝ የሆኑ መረጃዎችን ለመጠበቅና የላቀ የመረጃ ደህንነት ደረጃ ለማስፈን ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ያሳያል። እንዲሁም ዘመን ባንክ የመረጃ ደህንነት ስጋቶችን በውጤታማነት ለመለየት፣ ለመገምገምና ለማስተዳደር […]

ዘመን ባንክ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ አተረፈ! አጠቃላይ የሀብቱ መጠን 116 ቢሊየን ብር ደረሰ

ዘመን ባንክ በ2017/2018 (እ.አ.አ 2025/26) በጀት ዓመት 10.2 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ የሀብቱ መጠን 116 ቢሊየን ብር ደርሷል፡፡ የባንኩ ዓመታዊ የማኔጅመንት ስብሰባ ከሐምሌ 17 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደበት ወቅት ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ባደረጉት ንግግር፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የላቀ ውጤት መገኘቱን ገልጸው፤ ለዚህ ስኬት ለባንኩ የማኔጅመንት […]

ዘመን ባንክ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቀን ክብረ በዓል ላይ በአጋርነት ተሳተፈ::

ዘመን ባንክ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ባዘጋጀው የሀገሪቱ ብሔራዊ ቀን (ባስቲል ዴይ) ክብረበዓል ላይ በአጋርነት ተሳተፈ፡፡ በዝግጅቱ ላይ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የፈረንሳይ ዜጎችና ጥሪ የተደረገላቸው ከ900 በላይ እንግዶች ተገኝተዋል። ዝግጅቱ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት የፈረንሳይ አምባሳደር በሆኑት በሚ/ር አሌክሲስ ላሜክ የመክፈቻ ንግግር በይፋ የተጀመረ ሲሆን ዘመን ባንክ […]

ዘመን ባንክ ዓለም አቀፍ የሴቶች የዲፕሎማሲ ቀን ዝግጅት በአጋርነት ተሳተፈ።

ዘመን ባንክ የሴቶች በዲፕሎማሲ ኔትወርክ በኢትዮጵያ (WIDEN) አጋር በመሆን ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ዓለም አቀፍ የሴቶች የዲፕሎማሲ ቀንን በጋራ አክብሯል። የሴቶች በዲፕሎማሲ ኔትወርክ በኢትዮጵያ (WIDEN) ከዓለም አቀፍ የሥርዓተ-ፆታ ሻምፒዮናዎች ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ አምባሳደሮችን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችን፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መሪዎችን በጋራ አሰባስቧል፡፡ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ የሥርዓተ-ፆታ […]

የባንኮች ካፒታላይዜሽን፣ ውህደትና የተቋማት ግዢዎችን ለማሳካት ጠንካራ ተቋማዊ አቅምእንደሚያስፈልግተገለፀ

የባንኮች ካፒታላይዜሽን፣ ውህደትና የተቋማት ግዢዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ጠንካራ ተቋማዊ አቅም መፍጠር እንደሚያስፈልግ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ አስታወቁ፡፡ ዘመን ባንክ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ አስመልክቶ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ እንደገለፁት፤ ከሌሎች ባንኮች ጋር መዋሃድ ካፒታልን ለማሳደግ፣ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግና ብሎም ተወዳዳሪና ጠንካራ የፋይናንስ ተቋም ለመፍጠር ይረዳል፡፡ በአንፃሩ ተፎካካሪ […]

ዘመን ባንክ የአሰራር ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን ከኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገለፀ፡፡

ዘመን ባንክ የአሰራር ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን ከኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው የዘመን ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት በማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመጀመሪያ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ኢንስቲትዩቱ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ያበለፀጋቸውን የተለያዩ ሥርዓቶችና የሥራ እንቅስቃሴዎቹን በተመለከተ ለዘመን ባንክ አመራሮች ገለፃ […]

ዘመን ባንክ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በአረንጓዴ ፋይናንስ ትብብራቸውን አጠናከሩ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና ዘመን ባንክ የአረንጓዴ የፋይናንስ ሥርዓት ቴክኒካል ድጋፍ ፕሮግራም አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ፡፡ በመጋቢት 2016 ዓ.ም. በይፋ የተጀመረው ይህ የትብብር ፕሮጀክት የዘመን ባንክን በአየር ንብረትና ተያያዥ የአደጋ አስተዳደርና በአረንጓዴ ፋይናንስ ዘርፍ ያለውን አቅም ለማጠናከር ያለመ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ትብብሩ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ በፕሮግራሙ ማዕቀፍ ዘመን ባንክ በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ከዲኤአይ ግሎባል ጋር በመተባበር በየፋይናንስ […]

ዘመን ባንክ ለዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር አጋርነቱን አሳየ

ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) በአዲስ አበባ ባዘጋጀውና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የተወከሉ ተሳታፊዎች ለተገኙበት ኮንፈረንስ ዘመን ባንክ ግንባር ቀደም አጋርነትን አሳየ፡፡ የአፍሪካን አቪዬሽን ደህንነት፣ ተደራሽነትና ኦፕሬሽናል ብቃት ላይ በማተኮር የሚካሄደው ስብሰባ በስካይ ላይት ሆቴል ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በተከፈተበት ወቅት ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፣ አቶ አስራት […]

‘’ የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪን መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላል’’ አቶ ሚካኤል ፀጋዬ

የዘመን ባንክ ቺፍ ሆልሴል ባንኪን ኦፊሰር አቶ ሚካኤል ፀጋዬ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪን መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፁ፡፡ አቶ ሚካኤል ይህን የገለፁት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (አይኤቲኤ) የፎከስ አፍሪካ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ አቶ ሚካኤል በኢትዮጵያ እየተሻሻለ የመጣውን የፋይናንስ ሁኔታና በቀጥታ ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተመለከተ ማብራሪያ ያቀረቡ […]